ህክምናዎን በተመጣጣኝ ዋጋ አለም አቀፍ ጥራት ባላቸው የህንድ ሆስፒታሎች ያድርጉ

የጤናማ ህይወት ጉዞዎን ዛሬ ይጀምሩ!

ካንሰርን አንድላይ እናሸንፍ!
ታካሚዎች
9000 +
ምርጥ ሆስፒታሎች
+
ስመጥር ሃኪሞች
+

የኢትዮጵያውያን ታካሚዎች 1ኛ ምርጫ!

በህንድ የሚገኙ ምርጥ የካንሰር ሃኪሞች እና ሆስፒታሎችን ያግኙ

ሜዲካል ህክምናዎች

አጋር ሆስፒታሎቻችን ዘመኑ ያፈራቸውን ከቴክኖሎጂ ጋር የሚሄዱ ጥራታቸውን የጠበቁ እንደ TomoTherapy, Trilogy Tx Linear Accelerator, HDR Brachytherapy, and Total Body Irradiation (TBI) ያሉ የካንሰር ህክምናዎችን ርህራሬ ከተሞሉ የህክምና ባለሞያዎች ጋር ያቀርባሉ። እነዚህን ዘመን አፈራች መሳሪያዎች የካንሰሩን ደረጃ በትክክል ለማወቅ እና ትክክለኛውም የህክምና አካሄድ ለመወሰን እጅጉን ይረዳሉ።

ሰርጂካል ህክምናዎች

አጋር ሆስፒታሎቻችን ከቀላል ምርመራዎች እና ቅድመ መከላከል ህክምናዎች ጀምሮ እስከ ካንሰር ቀዶ ጥገና እና ማስታገሻ ህክምናዎች ድረስ አገልግሎት ይሰጣሉ። እነዚህ የህክምና ማዕከላት ዘመኑ ባፈራቸው የህክምና መሳሪያዎች የተደራጁ ሲሆኑ በዘርፉ ያሉ ስፔሻሊስቶችን እና ሮቦቲክ ቀዶ ጥገናን ጨምሮ ማስተናገድ የሚችሉ ናቸው። ሮቦቲክ የህክምና መንገዶች በአሁኑ ሰዓት እንደ ራስ እና አንገት፣ ቶራክስ እና ሳንባ፣ ታይሮይድ፣ ጂናኮሎጂካል፣ የጨጓራና ትራክት እና እንቅፋት እንቅልፍ አፕኒያ (OSA) ለመሳሰሉት የካንሰር አይነቶች መደበኛ የህክምና ምርጫ ነው።

የጨረር ህክምናዎች

የጨረር ህክምና ለተለያዩ የካንሰር አይነቶች እና ለሌሎችየተወሰኑ የህክምናዎች ወሳኝ የህክምና አማራጭ ነው።የጨረር ህክምና የካንሰር ሕዋሳትን ለማጥፋት ወይም ለመጉዳት እንደ ኤክስ ሬይ፣ ጋማ ጨረሮች፣ ኤሌክትሮን ጨረሮች ወይም ፕሮቶን የመሳሰሉ ከፍተኛ ሃይል ያላቸውን ሞገዶች ይጠቀማል። የጨረር ህክምና እንደ ኬሞቴራፕይ ሙሉ ሰውነት ላይ የጎኞሽ ጉዳት የማያሳይ በመሆኑ እና በውጤታማነቱ ምክንያት ለካንሰር ህክምና ተመራጭ ያደርገዋል። የጨረር ህክምና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እና የመሳካት እድሉ እየጨረ ያለ ሲሆን የጎንዮሽ ጉዳቶችን በመቀነስ ካንሰርን ለመዋጋት አስፈላጊ መሳሪያ ያደርገዋል።

አጋር ሆስፒታሎች 

ሃኪሞቻችን

የህክምና ሂደትዎን በኛ በኩል ሲያደርጉ እንደሚከተለው ነው

Step 1
ገፃችንን ወይም ቢሮአችንን ይጎብኙ

በድህረ ገፃችን ወይም  በማህበርዊ ሚዲያ ገፆቻችን በኩል ያነጋግሩን አልያም ቢሮአችን በአካል ይምጡ

Step 2
የህክምና ታሪክ መቀበል

ሃኪሞቻችን ከእርስዎ ተገቢውን መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ ለእርስዎ ትክክለኛ ከሆነው ሆስፒታል እና ሃኪም ጋር ያገናኝዎታል

Step 3
ለእርስዎ ብቻ የተዘጋጀ የህክምና እቅድ

ከስፔሻሊስት ሃኪሞቻችን ጋር በመሆን ለእርሶው ተገቢ የሆነውን እና በበጀትዎ ልክ ያለ የህክምና እቅድ ለማውጣት ነፃ የምክክር ጊዜ ይኖራል።

Step 4
ከሆስፒታሎች መረጃ መሰብሰብ

በ48 ሰአታት ውስጥ እስከ 7 ሆስፒታሎች ድረስ የህክምና አማራጮችን እና ዝርዝር ወጪዎችን ያካትተ መረጃ ያገኛሉ። የሚታከሙበትን  ሆስፒታል ከመረጡ በኋላ  ከሆስፒታሉ ቡድን ጋር ግልፅ ውይይት ይደረጋል።

Step 5
የጉዞ ዝግጅቶች

የህክምና ቪዛን፣ የበረራ አማራጮችን እንዲሁም ማረፊያ ቦታን ጨምሮ ሙሉ የህክምና ሂደቶችን እናስተካክላለን።

step 6
እንግዳ ተቀባይነት

መዳረሻችሁ ላይ የሚገኘው ቡድናችን ከአየር መንገድ ተቀብሎ ምቾትዎ እንደተጠበቀ ህክምናዎን እንዲያጠናቅቁ በሚያስፈልግዎት ሁሉ ይረዳዎታል።

Step 7
ህክምና እና ድጋፍ

ህክምናዎን ከእንከን የለሽ እንክብካቤ ጋር ከቤትዎ የወጡ ሳይመስሎት አጠናቀው ይመለሱ።

የታካሚዎቻችን ታሪክ

በካንሰር ህክምና ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

እንደ ካንሰሩ አይነት፣ አስፈላጊው ህክምና እንዲሁም ታካሚው እንደሚገኝበት ሁኔታ ምርጥ የሚባለው ሆስፒታል ይለያያል። ማናኪ ሄልዝ ኬር ሁልጊዜም ከሆስፒታሉ ይልቅ ሃኪሞቹን በጥንቃቄ መምረጥ አስፈላጊ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም እኛ ጋር ለሚመጡት እያንዳንዱ ታካሚዎቻችን እንደሚያስፈልጋቸው ህክምና እና ህመማቸው ስፔሻሊስት ሃኪሞችን በጥንቃቄ መርጠን እናገናአኛለን።

ህክምናዎን ከሃገር ውጪ ማድረግ ካሰቡ ከሚሄዱበት ሃገር “የህክምና ቪዛ” ማኘት ያስፈልጋል። ይህን ቪዛ ለማግኘት ሃገር ውስጥ ከሚታከሙበት ሆስፒታል የሚስፈልግዎትን የህክምና አይነት የሚገልፅ ደብዳቤ ያስፈልግዎታል። በተጨማሪም እንደሚሄዱበት ሃገር ሌሎች መሟላት የሚኖርባቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።

ለህክምና የሚወጣው ወጪ እንደ ህመሙ አይነትና አስፈላጊው ህክምና ከሰው ሰው ይለያያል። አብዛኞቹ ሆስፒታሎች ኬዙን ከተመለከቱ በኋላ ምን አይነት ህክምና እንደሚያስፈልግዎት እና ያህል ወጪ ሊያወጡ እንደሚችሉ ያሳውቃሉ። ታካሚዎች ከመሄዳእው በፊት ይህንን መረጃ ሆስፒታሉን በመጠየቅ ማግኘት ይችላሉ። 

ህክምናዎን ለማድረግ ከማናኪ ጋር ሲጓዙ ህክምናዎን ጨርሰው ወደ ሃገርዎ እስኪመለሱ ድረስ በራሳችን የእንግዳ ማረፊያ ይቆያሉ። ወይም ደግሞ እንደፍላጎትዎ የመረጡት ሆቴል ውስጥ የሚቆዩበእትን ሁኔታ እናመቻቻለን።

ታካሚዎች ወደ ውጪ ለህክምና ሲሄዱ የቤተሰብ አባል እንደ አስታማሚ አብሮ መሄድ ይችላል። ለዚም አስታማሚው የጎብኚ ወይም የአስታማሚ ቪዛ ለማግኘት መጠየቅ ይኖርባቸዋል። ማናኪ ሄልዝ ኬር ይህንን የጉዞ ሂደት ያመቻቻል።

ህክምናዎን ጨርሰው ከመመለስዎት በፊት በውጭ ሃገር ያሉት ሃኪሞች ሃገር ውስጥ ካሉት ሃኪሞች ጋር በመሆን የክትትል እቅድ ያወጣሉ። ማናኪ ሄልዝ ኬርም ከመመለስዎት በፊት የሚያስፈልጉትን መድሃኒቶች ይዘው የሚመጡበትን ሁኔታ ያመቻችልዎታል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ጥያቄዎች በውስጥ መስመር ያናግሩን

ከህክምና ባለሙያዎቻችን ጋር በመገናኘት ዛሬውኑ የህክምና ሂደትዎን ይጀምሩ!

Copyright © 2024 Manaaki Healthcare | Powered by Grow Medico | This site is not a part of the Facebook website or Facebook Inc. Additionally. This site is NOT endorsed by Facebook in any way. FACEBOOK is a trademark of FACEBOOK, Inc .
Scroll to Top